በኢትዮጵያ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 49 ከሆኑ ሴቶች መካከል 62 በመቶ የሚሆኑት አስተማማኝ የጤና አገልግሎት ለማግኘት እንደሚቸገሩ ተጠቆመ፡
የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር ባስጠናውና ይፋ ባደረገው የአውሮፓውያኑ 2024/25 የስነ-ህዝብ እና ጤና ዳሰሳ ጥናት ይህ የተገለጸ ሲሆን ለሕክምና የሚሆን ገንዘብ ለማግኘት መቸገር እና እስከ ጤና ተቋሙ ያለው ርቀት ለዚህ ችግር መንስኤ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
75 በመቶ የጤና አገልግሎት የማግኘት ችግሮች የሚታየው በደቡብ ኢትዮጵያ መሆኑን የአገልግሎቱ ጥናት ያሳየ ሲሆን ያልተማሩና ዝቅተኛ የገቢ ደረጃ ውስጥ ያሉ ሴቶች ለችግሩ ይበልጡን ተጋላጭ ናቸው ብሏል፡፡
በሌላ በኩል ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 49 ከሆኑ ሴቶች መካከል 26 በመቶ የሚሆኑት በሕይወት ዘመናቸው የአካል ወይም የጾታ ጥቃት እንደደረሰባቸው ጥናት አመላክቷል፡፡
አግብተው ከሚያውቁ ወይም የፍቅር አጋር ከነበራቸው ሴቶች መካከል 30 በመቶ የሚሆኑት በአጋሮቻቸው የተፈጸመ አካላዊ፣ ጾታዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ጥቃት ማስተናገዳቸውም በጥናቱ ተገልጿል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
