ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ገንዘብ ከሚያዋጡ ስምንት የደረጃ አንድ አገራት ዝርዝር ውስጥ መግባቷ ተገልጿል፡፡
ይህ የተገለጸው 49ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ወይም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መደበኛ ስብሰባ አዲስ አበባ በተካሄደበት ወቅት ነው።
ከዚህ ቀደም ሞሮኮ፣ ግብጽ፣ አልጄሪያ፣ ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ብቻ የነበሩበት የከፍተኛ መዋጮ የሚከፍሉ አገራት ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ፣ ኬንያና አንጎላ ተካተው በጠቅላላ ስምንት ሆነዋል ነው የተባለው፡፡
አፍሪካ ህብረት በአውሮፓውያኑ 2016 ሩዋንዳ ኪጋሊ ላይ ባደረገው ስብሰባ አባል አገራት ከውጭ በሚያስገቧቸው ምርቶች ላይ የ0 ነጥብ 2 በመቶ ታክስ በመሰብሰብ ለህብረቱ ገቢ እንዲያደርጉ መወሰኑ የሚታወስ ነው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
