InternationalNews

የስፔን መንግስት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ በትንሹ 60 ሺህ ስደተኞች ሰሜን አፍሪካዊቷን ሞሮኮን ተሻግረው የስፔኗ ሱዌታ ከተማ መድረሳቸውን ገለፁ፡፡

አብዛኛዎቹ ስደተኞች የሜዲተራንያን ባህር በዋና አቋርጠው በከተማይቱ መድረሳቸው ሲነገር ከእነዚህ ስደተኞች መካከል እስካሁን 34ቱ በባህር ላይ ህይወታቸው አልፎ አስክሬናቸው መገኘቱም ተሰምቷል፡፡

የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ሁኔታው ግልፅ የሉዓላዊነት ጥሰት እና ጥቃት መሆኑን ጠቅሰው መንግስታቸው ሁሉንም ስደተኞች ወደመጡበት ሞሮኮ ጠራርጎ ለመሸኘት እየተዘጋጀ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

ከተማይቱ ያላት ነዋሪዎች 83 ሺህ ብቻ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን የስደተኞቹ ቁጥር ከነዋሪዎቹ ለመብለጥም መቃረቡ ነው የተነገረው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv