የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞቹ ቁጥር 14 ነጥብ 7 ሚሊዮን መድረሱ ተነገረ።
ይህ የተነገረው የሳፍሪኮም ኩባንያ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርቱ ላይ ነው።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ካለፈው ሚያዝያ እስከ ሰኔ ወር 2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት 3 ወራት ውስጥ 1 ሚሊዮን ደንበኞች አፍርቶ አጠቃላይ የደንበኞቹ ቁጥር 14 ነጥብ 7 ሚሊዮን መድረሱ ነው የተነገረው።
የዳታ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር 11 ነጥብ 5 ሚሊዮን እና የድምጽ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር ድግሞ 12 ነጥብ 3 መግባቱን የሳፋሪኮም ሪፖርት ያሳያል።
በተመሳሳይ የኤምፔሳ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር መጨመሩ የተጠቆመ ሲሆን 5 ነጥብ 9 ሚሊዮን ደርሷል ነው የተባለው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
