የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የመንግስት ተቋማት፣ የግል ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች የጉግል ክሮም ማሰሻቸውን በአፋጣኝ ወደ አዲሱ ቨርዥን በማዘመን ሲስተሞቻቸውን ከሳይበር ጥቃት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል፡፡
አስተዳደሩ ይሄንን ማሳሰቢያ የሰጠው የጉግል ክሮም የደህንነት ቡድን 7 እጅግ አሳሳቢ የሆኑትን ጨምሮ 370 የደህንነት ክፍተቶች ላይ የሶፍትዌር ማስተካከያ ማድረጉን ማስታወቁን ተከትሎ ነው፡፡
አዲሱ የክሮም ማዘመኛ ከተጠቀሱት በተጨማሪ 71 ከፍተኛ፣ 170 መካከለኛ እና 122 ዝቅተኛ ደረጃ ያላቸውን የደህንነት ክፍተቶች ላይ ማስተካከያ ማድረጉ ነው የገለጸው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
