EthiopiaNews

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይሄን ያሉት በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል መርሃ ግብር በተመለከተ ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር በህዝባዊ ቁርጠኝነት እና ኢትዮጵያውያን በጋራ በመሆን አረንጓዴ እና ዘላቂነት ያለው ነገን መገንባት ይችላሉ በሚለው የጋራ እሳቤ እየተመራ ይበልጥ እየጠነከረ መቀጠሉን ነው በመልዕክታቸው ያመለከቱት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ ዘላቂ ዐሻራ ለማሳረፍ በጋራ የሚሰባሰቡበት ዓመታዊው የአንድ ጀምበር ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብራችን ነው ብለዋል።

ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር እንዲሁም ከኮፕ32 ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር በመሆን የራሳችንን ዐሻራ በማሳረፍ ለዚህ የጋራ ጉዞ የበኩላችንን አስተዋፅኦ አበርክተናል ሲሉም ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል ታላቅ ግብ ለማሳካት ኢትዮጵያውያን ቀኑን ሙሉ ጥረታችሁ እንዲቀጥል ሲሉመወ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።