EthiopiaNews

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊ ንቅናቄ በአዲስ አበባ በሰፊ ንቅናቄ እየተተከለ መሆኑን ተናገሩ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይሄን ያሉት ለአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብሩ 176 የሚሆኑ ቦታዎች መለየቱን እና የሚተከሉ ችግኞችን የጽድቀት መጠን በሚጨምር መልኩ በባለሙያ እየታገዘ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ባስታወቁበት መግለጫቸው ነው።

በሃሳብ አንድ ሆነን፣ በተግባራችን በእጆቻችን ችግኞችን ተክለን ውዷ ሃገራችንን አረንጓዴ እያለበስናት እንገኛለን ብለዋል ከንቲባዋ።

የምንተክለው ምግብ፣ ጥላ እና ውበታችንን ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች እየተከልን ያለነው ነገ በአየር መዛባት ምክንያት የሚወጣውን የብክለት፣ የጤና ችግር፣ የጎርፍ አደጋን አስቀድመን ለመከላከል ያለመ ነው ብለዋል።