የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2018 በጀት ዓመት ያልተጣራ 39 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።
ተቋሙ ይሄን ያስታወቀው የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ መድረክ ላይ ነው።
በበጀት ዓመቱ ተቋሙ ከነበረበት ኪሳራ ወጥቶ ይሄንን ትርፍ ወደማግኘት መሸጋገሩም ነው የተገለጸው፡፡
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በበጀት ዓመቱ ከመነጨው አጠቃላይ ኃይል ውስጥ 93 በመቶውን ለሀገር ውስጥ እና ቀሪ 7 በመቶውን ደግሞ ለጎረቤት ሀገራት አቅርቧል ያሉት።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የህዳሴ፣ የአይሻ እና የአሰላ ፕሮጀክቶችን በስኬት አጠናቆ ወደ ስራ ማስገባት መቻሉ የኢነርጂ ምርት ዕድገት እንዲመዘገብ ማስቻሉንም ተናግረዋል። መረጃው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘ ነው።
