InternationalNews

አፕል ቴሌግራም የድርጅቱን ጥብቅ የደህንት ቁጥጥር ህግጋትን በመጣስ የህፃናት ወሲባዊ ጥቃትን የሚደግፉ ይዘቶችን በመተግበሪያው ላይ እንዲለጠፍ በመፍቀዱ ከአፕ ስቶር እንዲጠፋ አድርጌዋለሁ ብሏል፡፡

ሆኖም ከሰዓታት በኋላ ቴልግራም እነዚህን ይዘቶች ከመተግበሪያው ላይ በማጥፋቱ እና አካውንት ባለቤቱንም ከመተግበሪያው ላይ በመሰረዙ ወደ አፕ ስቶር ዳግም እንዲመለስ መደረጉን አፕል አሳውቋል፡፡

በዓለም ዙሪያ ከ1 ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ቴሌግራም በገፁ ላይ የሚተላለፉ ይዘቶችን የሚቆጣጠርበት መንገድ እጅግ የላላ በመሆኑና በመተግበሪያው ላይ የሚከናወኑ ህገ ወጥ ተግባራት መበራከት ከበርካታ ሀገራት ክሶች እንዲበዝቡት አድርጓል፡፡