EthiopiaNews

በ2019 በጀት ዓመት 380 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቢሮው ይህን ያስታወቀው የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን በተወሰነው የጊዜ ገደብ በመክፈል እራሳቸውን ከቅጣትና ከወለድ እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ በሰጠበት ወቅት ነው፡፡

በመዲናዋ 456 ሺህ የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች መኖራችውን የጠቆመው ቢሮው ከእነሱም 9 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱን ገልጿል።

ቢሮው ባለፉት ሁለት ዓመታት ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብን ለማጠናከር እና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል የቴክኖሎጂ ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱንም አክሎ አስታውቋል፡፡