የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወልደ ገብረማርያም የኤየር ኢንዲያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው መሾማቸው ተነገረ።
ተወልደ ገብረማርያም ከፈረንጆች 2022 እስከ አሁን ድረስ የኤየር ኢንዲያ አየር መንገድ ስራ አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ ያሉትን ካምቤል ዊልሰንን በመተካት ነው የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው የተሾሙት።
የግዙፉ ታታ ኩባንያ ንብረት የሆነው ኤየር ኢንዲያ አየር መንገድ በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ሳቢያ ተግዳሮት ገጥሞት እንደነበር ያነሳው የሮይተርስ ዘገባ አዲሱ የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተቋሙን ትርፋማ ያደርጋሉ ተብለው እምነት ተጥሎባቸዋል ነው ያለው፡፡
