የየመኑ ሁቲ ታጣቂ ቡድን በቀይ ባህር ላይ ሲጓዝ በነበረ አንድ የሳዑዲ አረቢያ ነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሙን አሳውቋል፡፡
የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ ያህያ ሳሪያ በሰጡት መግለጫ የሚሳኤል ጥቃት የተፈጸመባት ነዳጅ ጫኝ መርከብ በቀይ ባህር የሳዑዲ አረቢያ ወደብ አቅራቢያ ስትንቀሳቀስ የነበረች ዋፋ የተሰኘች መርከብ ናት ብለዋል፡፡
ሁቲዎች ጥቃቱን መፈጸማቸውን ቢገልጹም በመርከቧ ላይ ስለደረሰው ጉዳት እስካሁን በይፋ የተባለ ነገር ባይኖርም ታጣቂ ቡድኑ ጥቃት ያደረሰባቸው መርከቦች ብዛትም 8 መድረሳቸው ነው የተገለጸው፡፡
