EthiopiaNews

ኢትዮጵያ በአፍሪካ በሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን የኢንተርፖል የአፍሪካ የሳይበር ስጋት ምዘና ሪፖርት አመላከተ፡፡

ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል የተቋቋመው ኢንተርፖል ባወጣው የ2026 ሪፖርቱ የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ እየተፋጠነ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተወሳሰበ ከመጣው የሳይበር ስጋት ጋር እየተጋፈጠች እንደምትገኝም ነው ያስነበበው፡፡

በመላው አፍሪካ በሳይበር ወንጀል ምክንያት የሚደርሰው ቀጥተኛ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት 5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር መድረሱን የጠቆመው ሪፖርቱ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ይህ ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑንም ነው የጠቀሰው፡፡

በአህጉሪቱ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያና ሴኔጋል ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ያለባቸው ሀገራት ስለመሆናቸው በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡