ይህ ክረምት በከንቱ እንዲያልፍ ሊፈቀድለት የማይገባ ትልቅ ዕድል ይዞ መጥቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኮርሶች በነጻ ለወጣቶች መቅረባቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል፡፡
ከስልጠናው የሚገኘው የምስክር ወረቀትም ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው በመሆኑ ወጣቶች የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በዛሬው እለትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እንዲሁም ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ጋር በመሆን ባህር ዳር ከተማ ገብተዋል።