የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አገራቸው በተናጥል በኢራን ላይ ጥቃት ልትከፍት እንደምትችል ተናገሩ።
ምንም እንኳን በኢራንና አሜሪካ መካከል የተከሰተውን ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት ጥረቶች እየተደረጉ ቢገኙም ኔታንያሁ ኢራን የኒውክለር ጦር መሳሪያ እንዳይኖራት ለማድረግ ማናቸውንም እርምጃ እንደሚወስዱ ነው የገለጹት፡፡
አሜሪካ የሀገራቸው ታላቅ ወዳጅ ሀገር መሆኗን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የእስራኤልን ደህንነት ለማረጋገጥ ሲባል ግን በኢራን ላይ በተናጥልም ቢሆን እርምጃ ከመውሰድ እንደማይመለሱ ገልጸዋል፡፡
ኔታንያሁ የኢራን አብዮታዊ ዘብ ኮማንደር አህመድ ቫሂዲ ኢራን የኒውክለር ጦር መሳሪያ መስራቷን እንደምትቀጥልበት መናገራቸውን አስታውሰው ሀገራቸው ይህ እንዳይሆን እንደምታደርግ ነው የገለጹት፡፡