InternationalNews

ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን ዳግም ለመክፈት ከኦማን ጋር እየተደረገ ያለው ድርድር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አሳውቃለች።

የኢራን ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኤስማኤል ባጌይ ስለስምምነቱ የሰጡት ዝርዝር ማብራሪያ ባይኖርም ሁለቱ ሀገራት ከስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረባቸውን ነው የጠቆሙት፡፡

ቃል አቀባዩ አክለውም ከኦማን ጋር የሚደረሰው ስምምምነት ብቻ በሆርሙዝ ሰርጥ ሰላማዊ የባህር ትራንስፖርትን አያረጋግጥም ያሉ ሲሆን የባህር ወሽመጡ ደህንነት አሜሪካ በኢራን ወደቦች ላይ የጣለችውን እገዳ ማንሳትና አለማንሳት ላይ ይመረኮዛል ብለዋል፡፡

ከቀናት በፊት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን በአፋጣኝ ካልከፈተች እጅግ ከባድ ጥቃት እንደሚጠብቃት ማሳሰባቸውም አይዘነጋም፡፡