EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2018 ዓ.ም 118 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱንና ገቢው ከእቅዱ አንጻር 102 ነጥብ 6 በመቶ መሆኑን ይፋ አደረገ።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ተቋሙ በበጀት ዓመቱ 20 ነጥብ 25 ቢልየን ብር ትርፍ ማኘቱንም አስታውቀዋል።

ተቋሙ በግብር መልክ ዘንድሮ ለመንግስት የከፈለው ከ12 ቢልየን ብር በላይ መሆኑን ጠቅሰው ይኸም አፈጻጸም ከ2017 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር 56 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ ተቋሙ ባደረገው ጥረት 664 ሺ 505 አዳዲስ ደንበኞች ማፍራቱን ከዚህ ውስጥ 205 የገጠር ከተሞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ተናግረዋል።