EthiopiaNews

የጉምሩክ ኮሚሽን 693 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ከሀምሌ 23 እስከ ሀምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 648.4 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 44.6 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 693 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን አሳውቋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አዳዲስ እና ልባሽ ጨርቆች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግብርና ምርቶች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ ማዕድናት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር አዋሽ፣ ድሬድዋ እና ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ በቅደም ተከተላቸውም 153 ሚሊዮን፣ 109 ሚሊዮን እና 106 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 30 ተጠርጣሪዎች እና 17 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጿል።መረጃው ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv