በሃገሪቱ 7 ነጥብ 4 ማግኒቲዩድ ሆኖ ትናንት የተመዘገበውን ከባድ ርዕደ መሬት ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል።
በአደጋው ከሞቱት 132 ሰዎች በተጨማሪ የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር ከ480 በላይ ደርሷል ተብሏል።
በርካታ ሰዎች አሁን ድረስ በፍርስራሽ ህንጻዎች ስር እንዳሉ ሲነገር የሟቾች ቁጥር በይፋ ከተገለፀውም በላይ ሊጨምር እንደሚችል ተነግሯል።
በአደጋው ከሞቱት በርካታዎቹ ሰዎች ቡና አብቃይ በሆነችው የሃገሪቱ የፔሬራ ግዛት መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
