ኢትዮጵያ የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎች የአመራር ፎረም ጉባኤ አስተናጋጅ እንድትሆን መመረጧ ተነገረ፡፡
ይህን በተመለከተም የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎች አመራር ፕሮግራም ዳይሬክተር ከሆኑት ከጃኒ ካማሊ ጋር ስለ ፕሮግራሙ አስፈላጊነት ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
በፕሮግራሙ ቀጣይነትም ውይይት አድርገናል ያሉት ሚኒስትሯ ፕሮግራሙ በሀገራችን ከተሞች ላይ ለውጥ ማምጣት ከጀመረ 4 ዓመታት አልፈዋል ብለዋል።
ፕሮግራሙ በዋናነት የከተሞችን ዲጂታላይዜሽንና የመረጃ አስተዳደር ማሻሻል እንዲሁም ከተሞች የውስጥ ገቢያቸውን አሳድገው በራሳቸው እንዲቆሙ እያገዘ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴርም ይህን የአፍሪካ ከንቲባዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ ከተሞች በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝመ ተገልጿል፡፡
