EthiopiaNews

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ከ16 መንግስታዊ ተቋማት ጋር በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።

በዚህ ስነ ስርዓት ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኃይማኖት ዘለቀ ስምምነቱ የሚዲያ ዘርፉን ለማጠናከር፣ የመረጃ ፍሰትን ለማሻሻልና በተቋማት መካከል ያለውን ቅንጅት ለማሳደግ ያለመ ነው ብለዋል።

በትብብሩ የዲጂታል ሚዲያ ልማት፣ የመረጃ ደህንነት፣ የሳይበር ስጋት መከላከልና የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀም ትኩረት እንደሚሰጣቸውም ገልጸዋል።

የመግባቢያ ሰነዱ በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚደገፍ ሲሆን በትብብሩ ከተካተቱት ተቋማት መካከል ብሔራዊ መረጃና ደህንነት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የፍትህ ሚኒስቴር፣ የመከላከያ ሚኒስቴር፣ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ፖሊስና የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ይገኙበታል።

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኮሚሽን፣ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በስምምነቱ ተካተዋል።

በተቋማቱ መካከል የሚኖረው ትብብር የሚዲያ ተቋማት የዲጂታል ለውጡን በተሻለ ሁኔታ እንዲከተሉ፣ የመረጃ ደህንነታቸውን እንዲያስጠብቁና ለህዝብ የሚደርሰው መረጃ ታማኝነትና ጥራት እንዲጠናከር ያግዘ\ል ነው የተባለው።