አብርሃም ሊንከን በተባለችው የአሜሪካ ግዙፍ ጦር መርከብ ለ250 ቀናት በግዳጅ ላይ የቆዩ ወታደሮች ሁኔታ እያነጋገረ ነው።
በርካታ የመገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ እንዳሉት የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከቧ ላይ ያሉት ወታደሮች ለረጅም ጊዜ በባህር ላይ በመቆየታቸው የምግብ እጥረትና የጥገና ቁሳቁስ ችግር እየገጠማቸው ነው።
ይህም የባህር ኃይል አባላቱን ለስነልቦና ችግር ሲዳርግ የአገሪቱ ፓርላማ አባላትም የትራምፕ አስተዳደር በአሁኑ ዘመቻ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ነው።
የአሜሪካ ወታደራዊ የዜና ምንጮች እንደሚሉት ደግሞ በተለያየ ጫና ውስጥ ያሉት ባህርተኞች በጭንቀት ከመርከቧ ወደ ባህር እየዘለሉ ነው።
