የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2ሺህ 212 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን አስታወቀ፡፡
በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 10 ዙር በረራ የተመለሱት 2ሺህ 210 ወንዶችና 1 ሴት እንዲሁም 1 ጨቅላ ህፃን ሲሆን ከተመላሾች መካከል 38 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ሚኒስቴሩ መስከረም 5/ 2018 አ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ94 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
ሚኒስቴሩ ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመተባበር እየሰራሁ ነው ብሏል።
