የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በመጪው የትምህርት ዘመን አንድ ተማሪ ከአቅሙና ከፍላጎቱ ጋር የተያያዘ አንድ የሙያ ዓይነት መርጦ መማር የሚያስችለውን ስርዓት ወደ ስራ እንደሚያስገባ ገልጿል፡፡
ቢሮው ይህን የገለጸው በመጪው የትምህርት ዘመን በ11ኛ ክፍል ለሚጀመሩ አዳዲስ የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ ዓይነቶችን በተመለከተ ባዘጋጀው የአተገባበር መመሪያ ላይ ነው፡፡
በትምህርት ሥርዓቱ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ እና ተማሪዎችን ለሥራው ዓለም ለማዘጋጀት ያለመ አዲስ የአተገባበር መመሪያ ማዘጋጀቱን የገለጸው ትምህርት ቢሮው በ2019 ዓ.ም ለ11ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚቀርቡ 11 የሙያ ዓይነቶችን በትምህርት ቤቱና በተማሪው ምርጫ ተግባራዊ እንደሚደረግም ነው የገለጸው፡፡
ባለፉት ጥቂት አመታት እንደ ግብርና፣ ጤና ሳይንስ፣ ኮንስትራክሽን እንዲሁም ኮምፒውተር ሳይንስ የመሳሰሉ የሙያ አይነቶች ለተማሪዎች ሲሰጡ መቆየታቸውን የገለጸው ቢሮው አሁን ደግሞ በሁለተኛ ዙር ለ11ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚቀርቡ 11 አዳዲስ የሙያ ዓይነቶችን ተግባራዊ ለማድረግ መመሪያ መዘጋጀቱን አመልክቷል።
በዚህ አዲስ የአተገባበር ሥርዓት ውስጥ የግንባታ፣ ማኑፋክቸሪንግ እና ቢዝነስ ሳይንስ ዘርፎች የተካተቱ ሲሆን አንድ ትምህርት ቤት እንደ አቅሙና እንደ አካባቢው ሁኔታ የተወሰኑትን የሙያ ዓይነቶች መርጦ ተግባራዊ እንዲሚያደርግም ነው የተጠቆመው፡፡
አንድ ተማሪ ከአቅሙና ከፍላጎቱ ጋር የተያያዘ አንድ የሙያ ዓይነት ብቻ መርጦ የሚማር ሲሆን፣ ይህም ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ሥራ ፈጣሪ ዜጎች እንዲሆኑና የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲደግፉ ለማስቻል ያለመ መሆኑም ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በመጪው የትምህርት ዘመን አንድ ተማሪ ከአቅሙና ከፍላጎቱ ጋር የተያያዘ አንድ የ
