InternationalNews

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ጃሬድ ኩሽነር በጋዛ ሰላም ዕቅድ ዙሪያ ከሀማስ ጋር ከተወያዩ በኋላ እስራኤል መግባታቸው ተነገረ።

ጃሬድ ኩሽነር ከሀማስ አመራሮች ጋር በሰላም ዕቅዱ አፈጻጸም ዙሪያ ከመከሩ በኋላ በተመሳሳይ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በዛሬው ዕለት ይመክራሉ ተብሏል፡፡

ባለፈው ወር የትራምፕ የጋዛ የሰላም ቦርድ ሀማስ ትጥቁን ሙሉ ለሙሉ ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን ቢያሳውቅም ባለፈው ሳምንት ደግሞ እስራኤል ይህንን የጋዛ የሰላም ዕቅድ ውድቅ ማድረጓን ማሳወቋ አይዘነጋም፡፡

ትላንትና ስምንት የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት እስራኤል ይህንን የጋዛ የሰላም ዕቅድ ውድቅ ማድረጓን በመቃወም የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡