InternationalNews

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው ከደቡብ ኮሪያ ጋር የምታደርገውን ዓመታዊ ወታደራዊ ልምምድ በእጅጉ እንደምትቀንስ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት ደግሞ ከሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን ጋር ያላቸውን መልካም ግንኙነት ለመጠበቅና ደቡብ ኮሪያ ሀገራቸው በኢራን ላይ የከፈተችውን ጦርነት ለመቀላቀል ፈቃደኛ ባለመሆኗ ነው ብለዋል፡፡

ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል የግል ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ በለጠፉት መልዕክት ደቡብ ኮሪያ ሀገራቸው ኢራን የኒውክለር ጦር መሳሪያ እንዳትታጠቅ ለማድረግ የከፈቱትን ጦርነት ባለመቀላቀሏ ቂም መያዛቸውን ያሳበቀ ጽሑፍ ለጥፈዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ከደቡብ ኮሪያ ጋር የሚደረገው ይህ ወታደራዊ ልምምድ ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅና ሀገራቸው ወጪውን ስትሸፍነው መቆየቷን አስታውሰው መሰሉ ልምምድም ፀብ አጫሪና ትክክለኛ ያልሆነ መልዕክት ለሌሎች ሀገራት ያስተላልፋል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡