የደቡብ አፍሪካው የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ሲብሪን በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ውስጥ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ፡፡
በኢትዮጵያ ያካሄደውን የገበያ ጥናት ተከትሎ ይሄንን እቅድ መያዙን የጠቀሰው ኩባንያው በሀገሪቱ የተደረጉ የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎች፣ እያደገ የመጣው የዲጂታል አጠቃቀም እና መንግሥት የፋይናንስ አገልግሎቶች ተዳራሽነትን ለማስፋፋት በሚያደርገው ጥረት ምክንያት በሀገሪቱ ለመሰማራት መወሰኑን ነው የገለጸው፡፡
ይሄንን እቅዱን ወደ ስራ ለማስገባት በኢትዮጵያ የአይሲቲ ቁሳቁስ አቅራቢ ተቋም ከሆነው ሞቲ ኢንጂነሪንግ ጋር አጋርነት መመስረቱን የጠቀሰው ተቋሙ ከክፍያ መሰረተ ልማት ባሻገር በሌሎች የዲጅታል እንቅስቃሴዎች ላይ እንደሚሰማራ መግለጹንም አይቲዌብ የተሰኘው የደቡብ አፍሪካ የሚድያ ተቋም ዘግቧል፡፡
