ብሪታንያ የዩክሬንን ጦርነት ሆን ብላ እንዲባባስ ታደርጋለች ስትል ሩሲያ ከሰሰች።
የሩሲያ ባለስልጣናት እንደሚሉት ብሪታንያ ለዩክሬን ድሮኖችን በመለገስ ሩሲያ እንድትጠቃ በማድረጓ ለዚህ ድርጊቷ የእጇን እንድታገኝ ትደረጋለች፡፡
ሩሲያ ይህን ያለችው አሁን አሁን ብሪታንያ ሰራሽ ድሮኖች በሩሲያ የውስጥ ግዛት በስፋት ሥራ ላይ መዋል በመጀመራቸው ነው ተብሏል፡፡
ብሪታንያ የዩክሬን የሽብር ተግባር ተሳታፊ በመሆን ልትዘልቅ አትችልም ሲሉ ነው የሞስኮ ባለስልጣናት ያስጠነቀቁት፡፡
ስለ ክሱ በቢቢሲ የተጠየቁት የብሪታንያ ባለስልጣናት ምንጊዜም ከዩክሬን ጎን እንቆማለን ነው ያሉት፡
