የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ የአገሪቱ መሪ ሆነው በድጋሚ ተመረጡ።
ፕሬዝዳንት ሂቺሌማ ለተጨማሪ አምስት ዓመት የተመረጡት የመራጩን ሕዝብ 60 ከመቶ ድጋፍ በማግኘት ነው።
የሂቼሌማ ድጋሚ መመረጥ በስፋት ይጠበቅ የነበረ ሲሆን ተፎካካሪያቸው ብሬን ሙንዱቤሌ 38 ከመቶ ድጋፍ አግኝተዋል።
ሌሎች 12 ዕጩዎች ትርጉም ያለው ድምፅ ሳያገኙ ተሸንፈዋል ነው የተባለው የአሁኑ ውጤት የወጣውም የ55 ዓመቱ ተፎካካሪ ሙንዴቤሌ ቀድመው ማስረጃ ባያቀርቡም ምርጫው ተጭበርብሯል ሲሉ በመቆየት በኋላም ምርጫውን ማሸነፋቸውን ካወጁ በኋላ ነው።
በምርጫው ውጤት መጭበርበር ውዝግብ ከተነሳ በኋላ ባለፈው ዓርብ አንዳንድ የተቃዋሚ አመራሮች ለእስር ተዳርገዋል።
