የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ባለቤት የሚሆኑበት አሰራር ወደ ተግባር መግባቱን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከመከላከያ ሚኒስቴር፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ጋር በአተገባበሩ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡
በመመሪያው መሠረት ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ሊያሟላ የሚገባው እና ለአንድ መኖሪያ ቤት የሚያስፈልገው ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን ተዘርዝሯል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ሊኖረው የሚችለው አንድ ቤት ብቻ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
