ፕሬዝዳንት ትራምፕ በካናዳ ላይ የጣሉትን የ50 ከመቶ የንግድ ታሪፍ ተግባራዊነት በሦስት ቀናት አራዘሙ።
ትራምፕ ለሦስት ቀናት የታሪፉን ትግበራ ያራዘሙት ሁለቱ አገራት ከአንዳች የንግድ ስምምነት ሊደርሱ በመቃረባቸው ነው።
ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ካናዳን ከአንዳች ስምምነት ድረሱ ካለበለዛ ታሪፉ አይቀሬ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ትራምፕ የታሪፍ ትግበራውን ያራዘሙት 20 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ የካናዳ ምርቶች ላይ የ50 ከመቶ ታሪፍ ሊጣል አንድ ቀን ሲቀረው ነው።
ሁለቱ አገሮች የታሪፍ እሰጣ ገባ ውስጥ የገቡ ሲሆን በዚህም የካናዳ ተሽከርካሪዎችና የአሜሪካ የአልኮል መጠጦች ከባድ ፈተና ገጥሟቸዋል።
ችግሩን ለመፍታት ፕሬዝዳንት ትራምፕና የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ በዚህ ሳምንት ብቻ ሁለቴ በስልክ መነጋገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
