InternationalNews

አረብ ኤምሬትስ ከኢራን የሁለት ቦለስቲክ ሚሳኤሎች ጥቃት ተሰንዝሮብኛል በሚል ከቴህራን ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት አቋረጠች።

ሁለቱ ቦለስቲክ ሚሳኤሎች ወደ ድንበሯ ቢተኮሱም በባህር ላይ መውደቃቸውን በመግለፅ ነው ኤምሬትስ ከእንግዲህ ከኢራን ጋር ምንም የንግድ ግንኙነት አላደርግም ያለችው።

አሁን አረብ ኤምሬትስ እርምጃውን የወሰደችው በአሜሪካና ኢራን መካከል ለ60 ቀናት ተደረሰ የተባለው የመግባቢያ ስምምነት ቀነ ገደብ በተጠናቀቀ ማግስት ነው።

በተያያዘ ዜና ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከእንግዲህ ኢራንን የማንበርክከው በአየር ድብደባ ሳይሆን በተራዘመ የጦር ስትራቴጂ ነው ማለታቸው ተሰምቷል።

ትራምፕ ይህን ያሉት ሆርሙዝን ለማስከፈት የተከተሉት ከባድ አየር ድብደባ ስልት ውጤት ባለማምጣቱ ነው ተብሏል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv