የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከእንግሊዝ የድርድር ቡድን ጋር የሚያካሂደው የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር ዛሬም በአዲስ አበባ መካሄዱን ቀጥሏል።
በትላንትናው ዕለት በተደረገው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ፤ ከ23 ዓመታት በላይ የወሰደውን የኢትዮጵያን የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር በ2026 መጨረሻ ለማጠናቀቅ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን አስመልክቶ ለእንግሊዝ የድርድር ኮሚቴ አባላት አብራርተዋል።
ሚኒስትሩ በንግግራቸው ኢትዮጵያ የልማት ፍላጎቷን ያገናዘበ ገንቢና መፍትሔ-ተኮር የገበያ ሁኔታ ማቅረቧን እና እስከ አሁን ከ11 ሀገራት ጋር ድርድር ማጠናቀቋን አረጋግጠዋል።
የእንግሊዝ መንግሥት ለኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት ለሚያደርገው ድጋፍና አጋርነት ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን እንዲሁም ድርድሩ ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
