EthiopiaNews

ኢትዮጵያን ጨምሮ በ10 የአፍሪካ ሀገራት የሕጻናት የሰውነት መቀጨጭ ሲገመገም አሁንም ችግሮች ቢኖርም ከሳህራ በታች ሀገራት ኢትዮጵያ መሻሻል አስመዝግባለች ተብሏል፡፡

ይህ የተነገረው የዓለም የጤና ድርጅት፣ ከተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ተቋም (ዩኒሴፍ) እና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን ችግሩን ለመከላከል ያለመ ጉባኤ በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ በ10 የአፍሪካ ሀገራት በአየርላንድ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ እየተሰራ የሚገኘው ስራ በተገመገመበት በዚህ መድረክ ከሰሀራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ከእስያ ቀጥሎ በዓለምአቀፍ ደረጃ ሁለተኛው ከፍተኛ የህጻናት መቀጨጭ ችግር ተመዝግቦባቸዋል ተብሏል፡፡

በዓለም ላይ ዕድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች ከሆኑ ህፃናት ሞት ውስጥ እስከ 45 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከምግብ እጥረት እና ከመክሳት ጋር የተያያዘ እንደሆነ የተጠቀሰ ሲሆን በችግሩ በብዛት የተጠቁ ስፍራዎች መካከል ደቡብ እስያ ከ 25 ሚሊዮን በላዩ የሚገኙበት እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡

በተለይም በምስራቅና በማዕከላዊ አፍሪካ በድርቅ፣ በግጭት እና በምግብ ዋስትና እጥረት ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህፃናት ለችግሩ መጋለጣቸው የተገለጸ ሲሆን በአንጻሩ በኢትዮጵያ ግን ችግሩ ከነበረበት 11 ከመቶ አሁን ወዳለበት 5 ከመቶ መውረዱ ነው የተጠቆመው፡፡

ኢትዮጵያ ይህንን የከፋ የአመጋገብ ችግር ለመቅረፍ እንደ ሰቆጣ ቃልኪዳን ያሉ ፕሮግራሞችን በመቅረጽ ችግሩን ለመቀነስ እየሰራች እንደሆነም ነው የተነገረው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv