የትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 የትምህርት ዘመን ተጨማሪ አራት የፌደራል የአዳሪ ትምህርት ቤቶችን ወደ ስራ ማስገባቱ ገለጸ፡፡
ሚኒስቴሩ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል በማለም የአዳሪ ትምህርት ቤቶች የማስፋፋት ስራ ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
መግለጫውን የሰጡት የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረ ሕይወት በ2019 የትምህርት ዘመን ተጨማሪ አራት የፌዴራል የአዳሪ ትምህርት ቤቶች በባህርዳር፣ አርባምንጭ፣ ድሬደዋ እና አሶሳ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በባለፈው ዓመት የትምህርት ዘመን አምስት የፌዴራል አዳሪ ትምህርት ቤቶች ማለትም ወሊሶ፣ ቡኢ፣ ጅግጅጋ፣ ቦንጋ እና ጋምቤላ ተማሪዎችን በመቀበል እያስተማሩ እንደሚገኙም ተናግረዋል።
የስምንተኛ ክፍል ፈተናን ከ80 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች የእድሉ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ እና ሆኖም ከአገሪቱ ጠረፋማ አከባቢዎች ለሚመጡ የተለየ ማበረታቻ እንደሚሰጥም ነው የተነገረው፡፡
በአዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ለመግባት ትምህርት ሚኒስቴር ፖርታል ላይ በመግባት መመዝገብ እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
