EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው በቀረቡ ምክረ ሀሳቦች ላይ የተጠናቀረው የመጨረሻ ሰነድ ነገ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ለሁሉም ተመካካሪዎች በጋራ እንደሚቀርብ አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገብረሥላሴ ይሄን ያሉት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ ከስምንቱም ቡድኖች የቀረበውን ምክረ ሀሳብ ለማጣጣም የተቋቋመው 120 አባላት ያሉት አጠናቃሪ ቡድን በጥንቃቄ ሲሰራ ቆይቶ እስከ ትናንት ምሽት ድረስ አንድ ወጥ የሆነ ሰነድ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ኮሚሽነሯ የተዘጋጀው ሰነድ ዛሬ ጠዋት ለየስምንቱ ቡድኖች የቀረበ መሆኑን ገልፀው ቡድኖቹ ሰነዱን አዳምጠው የመጨረሻ ግብዓትና አስተያየት እየሰጡ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ አጠናቃሪ ቡድኑ ዛሬ ማምሻውን እነዚህን የተሰበሰቡ አስተያየቶች በማካተት የመጨረሻውን ሰነድ አጠናቆ እንደሚያዘጋጅ ጠቁመዋል።

ኮሚሽነሯ ህዝቡ አንዳንዶች የሚያሰራጩትን የተዛባ መረጃ በመስማት እንዳይወዛገብ እና ለትክክለኛ መረጃዎች የኮሚሽኑን መግለጫዎች ብቻ እንዲከታተል አሳስበዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv