EthiopiaNews

በከፍተኛ የሰብዓዊ ዕርዳታ እና የፋይናንስ እጥረት ምክንያት፣ የኢትዮጵያ መንግሥትና ዓለም አቀፍ ተቋማት በሀገሪቱ የሚገኙ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ራሳቸውን እንዲችሉ ትኩረት ማድረጋቸው ተነገረ፡፡

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶችና የሰብዓዊ ዕርዳታ ቀንን አስመልከቶ ሮይተርስ ባወጣው ዘገባ  በኢትዮጵያ በሚገኘው የኡራ የስደተኞች ጣቢያ የሚኖሩ ስደተኞች እየቀነሰ የመጣው የዕርዳታ መጠን ፈታኝ ሁኔታ ደቅኖባቸዋል ነው ያለው፡፡

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በሚቀጥሉት ስድስት ወራት በኢትዮጵያ የሚያደርገውን የእርዳታ እንቅስቃሴ ለማስቀጠል 83 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገደማ እንደሚያስፈልገውም ነው የተጠቆመው፡፡

ይህ የገንዘብ እጥረት በስደተኞች የዕለት ተዕለት ሕይወት ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ ማሳደሩ የተገለፀ ሲሆን ስደተኞቹ በራሳቸው እንዲቆሙ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv