InternationalNews

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሆርሙዝ ሰርጥ አዲሱ የአሜሪካ ግዛት ነው ሲሉ አነጋጋሪ አስተያየት ሰጡ።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ይሄን አነጋጋሪ አስተያየታቸውን ይፋ ያደረጉት በትሩዝ ሶሻል የግላቸው የማህበራዊ ገፅ ነው።

ኢራን ትራምፕ የሆርሙዝ ሰርጥ የአሜሪካ ግዛት ነው በሚል ይፋ ያደረጉት አስተያየት ተጨባጭ መሰረት የሌለው የተጋነነ ስትል አጣጥላለች።

የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካዚም ጋሪባባዲ የትራምፕ አስተያየትን በፅኑ አውግዘው ሃገራቸው ለዚሁ ስህተት በቂ እርምት ትሰጣለች ብለዋል።

ይህ የሁለቱ ሃገራት አዲስ ውዝግብ የተሰማው የዋሽንግተን እና የቴህራን ድርድር በቆመበት ጊዜ ነው ሲል የዘገበው አርቲ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv