EthiopiaNews

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በብልሹ አሰራር የተሳተፉ በ216 ሠራተኞች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ የዲሲፕሊን እርምጃ መወሰዱን አስታውቋል።

ቢሮው ይሄን ያለው የተጠናቀቀውን የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ነው።

እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል የ6 ሠራተኞች የቅጥር ውል ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ነው የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የገለፀው።መረጃው ከአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የተገኘ ነው።