የዘንድሮው የመውሊድ በዓል ማክሰኞ ነሀሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጂድ እንደሚከበር ተገለፀ፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ1 ሺህ 501ኛውን የነቢዩ መሀመድ ልደትን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።
መውሊድ ነቢዩ መሀመድ የተወለዱበት ቀን የሚዘከርበት ሲሆን የዚህ ዓመት የመውሊድ በዓል የፍትሁ ነብይ በሚል መሪ ቃል እንደሚከበርም ተነግሯል፡፡
መውሊድን ማክበር የሚፈልግ ሁሉ እለቱን ነብዩን እያሰበ ሰላምና ወንድማማችነትን እንዲሁም ይቅር መባባልን በመረዳት ሊሆን እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
መውሊድን ማክበር የማይፈልግም ፍላጎቱ የተጠበቀ እንደሆነ የተጠቆመ ሲሆን ይህ ሙስሊሙን ማህበረሰብ የሚከፋፍል ሊሆን እንደማይገባም ተገልጿል፡፡
ይህ እንዳለ ሆኖ ህዝበ ሙስሊሙ የሀገራዊ ምክክር ሂደት ውጤታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አዎንታዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
