EthiopiaNews

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከአያት 49 ወደ ፊጋ በሚወስደው መንገድ ላይ 72 ድልድይ አካባቢ ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ መንገዱ በከፊል ለትራፊክ ዝግ እንደሚደረግ አስታውቋል።

መንገዱ በከፊል ለትራፊክ ዝግ የሚሆነው የመንገድ ጥገና ሥራ ለማካሄድ መሆኑን ባለስልጣን መ/ቤቱ ገልጿል።

ስለሆነም አሸከርካሪዎች ጥንቃቄ በማድረግ እንዲተላለፉ እና አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።መረጃው ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የተገኘ ነው።