EthiopiaNews

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 494 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 12 ዙር በረራ ዜጎቹ ወደ አገራቸው የተመለሱት፡፡

‎መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ96 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

‎መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከል ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመሆን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሚኒስቴሩ ገልጿል።