የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም ለሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺህ 501 ኛ የነብዩ ሙሐመድ የልደት መታሳቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን አስተላልፏል፡፡
ጉባኤው በዓሉን ስናከብር በተለመደው ኢትዮጵያዊ የመረዳዳት ባህላችን መሰረት በሕመም አልጋ ላይ፣ በሕግ ጥላ ስር በአጠቃላይም በችግር ውስጥ የሚገኙትን ወገኖቻችንን በመጠየቅ እና በማበረታታት፣ ያለንን በማካፈል ሊሆን ይገባል ነው ያለው፡፡
አክሎም ለአገራችን ኢትዮጵያ ሰላም፣ ለሕዝባችን አንድነት እና በረከት ከልብ የሆነ ዱዓ በማድረግ እንዲሆን በታላቅ አክብሮት ጥሪውን አቅርቧል፡፡
