InternationalNews

አሜሪካ በኢራን ላይ ማዕቀብ ለመጣል መዛቷን ተከትሎ የኢራን ገንዘብ የሆነው ሪያል ዋጋው ክብረወሰን በተባለ ደረጃ መውደቁ ተሰምቷል፡፡

አሜሪካ በወደቦቿ ላይ በጣለችው ክልከላ እና በበፊቶቹ ማዕቀቦች ምክንያት የኢራን ገንዘብ ከዶላር አንጻር ዋጋው በከፍተኛ ደረጃ መውደቁ አይዘነጋም፡፡

አሁን ላይ የኢራን ማዕካለዊ ባንክ አንዱን የአሜሪካን ዶላር በ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የኢራን ሪያል እየመነዘረ ቢሆንም በሀገሪቱ ጥቁር ገበያ ላይ አንድ ዶላር 2 ሚሊዮን ሪያል እየተመነዘረ ነው ተብሏል፡፡

የኢራን ገንዘብ መውደቅን ተከትሎ የሀገሪቱ ዜጎች መሰረታዊ ሸቀጦችን ለመግዛት እየተቸገሩ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን ለአብነት ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ እንኳን ሩዝ የ60 በመቶ እንዲሁም ስጋ የ150 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱ ተሰምቷል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv