የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን የ7 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማዕቀፍ ማፅደቁ ተገለፀ፡፡
ይህ ድጋፍ ዩክሬን የአየር መቃወሚያ እና የሚሳኤል መከላከያ እንዲሁም የሚሳኤል፣ ተቶካሾች እና ራደርን የመሳሰሉ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንድታገኝ ያስችላታል ተብሏል፡፡
በዩከሬን 35ኛ ዓመት የነፃነት በዓል ላይ ንግግር ያደረጉት የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮንደርላየን አውሮፓውያን ለዩክሬን የሚሰጡት ድጋፍ መቼም ቢሆን የማይቋረጥ እና ጠንካራ ነው ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቷ አክለውም ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ያፋፋመችበት ወቅት ነው ያሉ ሲሆን ለኬይቭ የሚደረገው ድጋፍ ሀገሪቱ ከዚህ የሞስኮ ጥቃት እራሷን እና ህዝቧን እንድትጠብቅ የሚያደርግ ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
