ብሪታኒያ የሩሲያን ዛቻ ችላ በማለት ለዩክሬን የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አሳወቀች፡፡
የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርናሀም በዩክሬን በነበራቸው ይፋዊ ጉብኝት ወቅት ይህንን ያሉ ሲሆን ዩክሬን የራሷን የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤል ማምረት እንድትችልም የመሳሪያውን ንድፍ የሚያሳይ ሰነድ ለኬይቭ አበርክተዋል፡፡
ሩሲያ ይህ የብሪታኒያ ድርጊት በእሳቱ ላይ ቤንዚን እንደማርከፍከፍ ይቆጠራል ስትል ያወገዘች ሲሆን ብሪታኒያ በቀጥታ በዩክሬን ጦርነት ውስጥ እየተሳተፈች መሆኑንም ገልጻለች፡፡
ሩሲያና ዩክሬን አንዱ በአንዱ ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት አጠናክረው መቀጠላቸው ሲነገር ዩክሬን በሩሲያ ጥቃት 5 ዜጎቿ መሞታቸውን የገለጸች ሲሆን ሩሲያም በኬይቭ ጥቃት 3 ታዳጊዎች መሞታቸውን አሳውቃለች፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
