የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ለጀማሪ ኢንቨስተሮች በሚል ሀሰተኛ መረጃ በማዘጋጀት ብር እየሰበሰቡ ካሉ አጭበርባሪዎች ህብረተሰቡ እራሱን እንዲጠብቅ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አሳሰበ።
ባለስልጣን መ/ቤቱ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ለጀማሪ ኢንቨስተሮች በሚል ሀሰተኛ መረጃ አዘጋጅተው በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በማስተዋወቅ ብር እየሰበሰቡ ያሉ አጭበርባሪዎችን እንደደረሰባቸው ገልጿል።
መ/ቤቱ በጉዳዩ ላይ ክትትል እንደሚያደርግ እና እና ህጋዊ እርምጃዎች እንደሚወስድ ገልፆ ህብረተሰቡ ከመሰል አሳሳች መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል።መረጃው ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
