EthiopiaNews

ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚወስዱት እርምጃዎች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገልጸዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ይህን ያሉት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ በጀመረው 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠና ኮሚቴ ጉባኤ መክፈቻ ላይ በተንቀሳቃሽ ምስል ባስተላለፉት መልዕክት ነው፡፡

በዚሁ ጊዜም ኢትዮጵያ የማርበርግ ወረርሽኝን በ90 ቀናት ብቻ መቆጣጠርና ማጥፋት መቻሏ የአፍሪካውያን የመተግበር አቅም እያደገ ለመምጣቱ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ርዕሰብሄር ታዬ አጽቀስላሴ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር መሀመድ ያኩብና የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባን ጨምሮ ከ47ቱ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ አባል ሀገራት የተውጣጡ የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች፣ የጤና ባለሙያዎችና የልማት አጋሮች ታድመዋል።

እስከ ነሃሴ 22 ቀን 2018ዓ.ም ድረስ በሚካሄድው ጉባኤው በአፍሪካ ዘላቂ የጤና ፋይናንስና ዲጅታል የጤና ስርዓት መገንባት፣ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ፣ የጤና ባለሙያዎች አቅም ግንባታና የሀገር ውስጥ ምርቶችን ማሳደግ ላይ ይመከራል ተብሏል፡፡