በኢትዮጵያ 210 ሺህ አርሶ አደሮችን የአየር ንብረት ለውጥ የመድህን ሽፋን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ4 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ።
ፕሮጀክቱ ይፋ የተደረገው በአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ እና በአለም የምግብ ፕሮግራም መሆኑ ነው የተነገረው፡፡
ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ የሚገኙ 210 ሺ አርሶ አደሮች በአየር ንብረት ለውጥ ችግሮች የሚደርስባቸውን ጉዳት እንዲቋቋሙ የሚደግፍ እንደሆነ የአለም የምግብ ፕሮግራም ገልጿል።
የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ጌልሶሚና ቪጂሊዮቲ ባንኩ በኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ችግሮች ሳቢያ ተጎጂ የሆኑ አርሶ አደሮች የመድህን ሽፋን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ መረጃው ከአለም የምግብ ፕሮግራም የተገኘ ነው።
