የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በትላንትናው ዕለት ባካሄደው የ125 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ሁለት ባንኮች ብቻ ማሸነፋቸው ተገለጸ፡፡
በውጭ ምንዛሪ ጨረታው 5 ባንኮች ብቻ መሳተፋቸውን የገለጸው ብሄራዊ ባንክ በጨረታው በተሳተፉ ባንኮች የታየው የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት 170 ሚሊዮን ዶላር መሆኑንም ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል፡፡
በጨረታው አንዱ የአሜሪካ ዶላር በ160 ብር ከ20 ሳንቲም የተሸጠ ሲሆን ይህ የጨረታ ውጤት ባንኩ በቅርቡ አካሂዶት በነበረው ጨረታ ከተመዘገበው ውጤት ጋር ተቀራራቢ ነው፡፡
ባንኩ ባለፈው ሳምንት ባካሄደው የ500 ሚሊዮን ዶላር ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንዱን ዶላር በ160 ብር ከ21 ሳንቲም መሸጡ ይታወሳል።
በዚሁ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 22 ባንኮች ተሳትፈው ሃያ አንዱ ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን ከ710 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት አሳይተው ነበር፡፡
